Home
Welcome to the Frontpage
ምሥጢረ ሥላሴ PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Wednesday, 26 February 2014 17:41

ምሥጢረ ሥላሴ

ሐዋርያ ወንጌል ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ “ወባሕቱ በቤተ ክርስቲያን እፈቅድ ኀምስተ ቃላተ እንግር በልብየ = ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን አምስት ቃላትን ልናገር በልቤ እሻለሁ“ ቆሮ፲፬፲፱ እንዳለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከውቅያኖስ የጠለቀውን ከነፋስ የረቀቀውን ትምህርተ ክርስትና በክቡር ደሙ ከዋጃት ከማይነጥፍ ከክርስቶስ ኢየሱስ ቃል ምንጭነት የታመኑ ባለሟሎቹ ሐዋርያት ቀድተው እንዳስረከቧት አዕማድ በተባሉ አምስት ምሥጢራት ከምላቱ ሳይጎድል ከስፋቱ ሳይጠብ እንደ ወርቅ እንክብል በጠሩ ኅብረ ቃላት ጠቅልላ ታስተምራለች። አምስት ምሥጢራት የተባሉትም

፩. ምሥጢረ ሥላሴ .  ምሥጢረ ሥጋዌ . ምሥጢረ ጥምቀት . ምሥጢረ ርባን . ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ናቸው።

ዓምድ ማለት ሙሰሶ ማለት ነው፥ አዕማድ በብዙ ፤ አዕማድ መባላቸው ሙሰሶ ቤትን ማዕበል እንዳይጥለው ነፋስ እንዳይገፋው እንደሚያጸና እኒህም ልቡናን በኑፋቄ እንዳይታወክ ከክህደት ከቀቢጸ ተስፋ እንዳይደርስ በእምነት በተስፋ የሚያጸኑ ስለሆኑ ነው። ሙሰሶ የሌለው ቤት ነፋስ ሲገፋው ይወድቃል ትምህርተ ሃይማኖትም ተምሮ ያላወቀ ሰው በጥርጥር በክህደት በሃይማኖት ከሚገኝ ጸጋና ክብር ይወጣል። ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ከሁሉ አስቀድማ ለወጣንያን ለማዕከላውያን በሚረዳቸው መጠን እኒህን ምሥጢራት ታስተምራለች። ምሥጢራት መባላቸውም ምሥጢር ለታመነ እንጂ ለሁሉ እንደማይነገር በክርስቶስ አምላክነት ወደማመን ለመጡ እንጂ በክህደት በአምልኮ ጣዖት ላሉ ለአሕዛብ ለአረማውያን የሚነገሩ ቢነገሩም በምር የሚረዱ ስላይደሉ፤ ዳግመኛም ለአእምሮ የረቀቀ ነገር ግን እውነት መሆኑ የታመነ ዕፁብ ዕፁብ ተብሎ በዕፁብ የሚወሰን በኅሊና መመራመር ግን የማይወሰን ድንቅ የሆነው ሁሉ ምሥጢር እንዲባል ሰው ዕፁብ ዕፁብ ብሎ በማመን የሚቀበላቸው እንጂ በመመራመር የማይወስናቸው ድንቅ እውነታዎች ስለሆኑ ነው።

Read more...
 
"ክቡር አውስቦ በኵለሄ .. ጋብቻ በሁሉ ዘንድ የከበረ ነው" ዕብ ፲፫፥፬ PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Sunday, 19 January 2014 16:29

"ክቡር አውስቦ በኵለሄ .. ጋብቻ በሁሉ ዘንድ የከበረ ነው" ዕብ ፲፫፥፬


(ጥር 5 ቀን 2006 ዓ/ም) የደብራችን መደበኛ አገልጋይ ዲ/ዶ/ር ሄኖክ ፍቅሬ የጋብቻ ስነ ሥርዓታቸውን በሥርዓተ ተክሊል ፈጸሙ። ለበርካታ ዓመታት በልዩ ልዩ የአገልግሎት ዘርፍ አመርቂ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩትና አሁንም በትጋትና በትዕግሥት ከመደበኛ የግል ሥራቸው በተጓዳኝ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ጊዜያቸውን ሰጥተው በማገልገል ላይ ያሉት ዲ/ዶ/ር ሄኖክ ከወ/ሪት አስማረች ዘውዴ ጋር ጋብቻቸውን የፈጸሙት ጥር 3 ቀ 2006 ዓ/ም በታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም ሲሆን ሥርዓተ ተክሊሉን የመሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ የጋብቻን ክቡርነት በማስረዳት ትዳራቸው የተባረከ ትዳር እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።

Last Updated on Monday, 20 January 2014 11:30
Read more...
 
“እስመ ኢየሱስ ክርስቶስ መጽአ ውስተ ዓለም ከመ ያድኅኖሙ ለኃጥአን ... ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአተኞችን ሊያድን ወደ ዓለም መጥቷልና“ PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Monday, 06 January 2014 20:35

“እስመ  ኢየሱስ ክርስቶስ መጽአ ውስተ ዓለም ከመ ያድኅኖሙ ለኃጥአን ... ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአተኞችን ሊያድን ወደ ዓለም መጥቷልና“ ፩ጢሞ ፩፥፲፭

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ቸርነትና ይቅርታ የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ ፥ ዓለማትን የፈጠረ ፥ ቀዳማዊና ደኃራዊ በአንድነቱ ምንታዌ በሦስትነቱ ርባዔ ሳይኖርበት እንደባለጸጋ በሀብት እንደ ነገሥታት በጉልበት እንደ ጣዖት በሐሰት ያይደለ ለንጽሐ ባሕርዩ ለጽንዐ አምልኮቱ በሚገባ እውነተኛ ምስጋና እርሱን ለማመስገን በሚተጉ በመላእክት ለአምልኮቱ በሚቀኑም ቅዱሳን ሰዎች አንደበት ሲቀደስ ሲወደስ የሚኖር ቅዱስ ቡሩክ ሕያው አምላክ እግዚአብሔር እንኳን በሰላምና በጤና ጠብቆ ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ!

በክርስቶስ ኢየሱስ ስም አምነንና ተጠምቀን ከስሞችም በላይ በሆነ ስሙ ክርስቲያን ተብለን ተላውያነ ክርስቶስ ሆነን የምንኖር ምእመናን በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ሳናቋርጥ በየዓመቱ በምስጋናና በፍጹም ደስታ ከምናከብራቸው ዐበይት በዓላት አንዱ በዓለ ልደት ነው። ይህንን በዓል የጌታ ከድንግል መወለድ በታወቀባት ሌሊት የሰማይ መላእክትና ምድራውያን እረኞች “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ ... በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ፍቅሩ ለሰው ልጆች ሆነ“ ብሎ በመዘመር ፤ ግሑሳንም ከእንስሳት ምልክቱን ተረድተው “ዮም ተወልደ ለነ ከሣቴ ብርሃን ፥ ዮም ተወልደ ለነ መድኃኔዓለም“ ብሎ በማወደስ ፥ በአጸደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳንም ትንቢት የተነገረለት ሱባዔ የተቆጠረለት መድኅን ተወለደልን ብሎ በማመስገን አክብረውታል። ሉቃ ፪፥፲፬

Read more...
 
ምእመናን ለሕንፃ ቤተክርስቲያን ግዢ ከ25 ሺ ዩሮ በላይ ለገሱ PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Thursday, 19 December 2013 17:25

ምእመናን ለሕንፃ ቤተክርስቲያን ግዢ ከ25 ሺ ዩሮ በላይ ለገሱ

ታኅሣስ 2006 ካስል (ጀርመን)- በጀርመን አገር  የሚገኘውን የካስል ደብረ ቀራንዮ መድኔዓለም የራሱ ሕንፃ ቤተክርስቲያን እንዲኖረው ለማስቻል እመናን ከ25 ሺ ዩሮ በላይ ለመለገስ ቃል ገቡ።

«ኑ የእግዚአብሔርን ቤት እንሥራ» ይላል ቅዱስ ቃሉ። ይህን መሠረት አድርጎ ከአራት ወራት በፊት የተቋቋመው የደብሩ ሕንፃ ግዢ ማኅበር ባካሄዳቸው የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ከ25 ሺ ዩሮ በላይ ጥሬ ገንዘብና የቃል ኪዳን ሰነድ ማሰባሰብ ችሏል።

‘‘እኁድ ቤተክርስቲያኑን እንፈልገዋለን፤ ቅዳሜ ጠዋት 10 ሰዓት ላይ ቤተክርስቲያኑን ለቃችሁ ውጡ፤ ዕጣን ማጨሳችሁን አልወደድነውምና ሌላ ቦታ ብትፈልጉ ይሻላል፤ ወዘተ“ ከሚሉት የተለመዱ የሕንፃ ቤተክርስቲያን አዋሾቻችን ንግግሮች ለመሸሽ፤ ሥርዓቱን የጠበቀ አገልግሎት በተሟላ ሁኔታ ለመስጠት፤ ብሎም ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በሀገረ ጀርመን የራሷ የሆነ ቅሪት እንዲኖራት በማሰብ ነው ማኅበሩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች በመቅረፅ አሐዱ ብሎ ሥራውን የጀመረው።

Read more...
 
« StartPrev12345678910NextEnd »

Page 7 of 12

Who's Online

We have 12 guests online

ሌሎች ድረ ገጾች

Featured Links:

feed-image Feed Entries


Powered by Medhanealem.