Home
Welcome to the Frontpage
የአምላካችን የመድኃኔዓለም ዓመታዊ በዓል ወዕረፍቱ ለአባ መባአጽዮን በካስል ደ/ቀ/ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ። PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Friday, 15 November 2019 12:30

የጌታችን የመድኒታችን የአምላካችን የመድኃኔዓለም መታዊ በዓል ወዕረፍቱ ለአባ መአጽዮን በካስል ደ/ቀ/

መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ።

በአንድ ዓመት ውስጥ አጥቢያው ለሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ግዢ ከተበደረው የባንክ እዳ ግማሹን ተመላሽ ማድረጉም ተገልጿል።


ዳር ፩- ፳፻፲፪ ዓ.ም (ካስል-ጀርመን)የዘንድሮው የጥቅምቱ መድኃኔዓለም ዓመታዊ በዓል ወዕረፍቱ ለአባ መአጽዮን

በካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የተከበረው ጥቅምት ፳፱ እና ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም ነው።


በበዓሉ ላይ ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የመጡ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ካህናት፣ ዲያቆና

እና በርካታ መናን ተገኝተዋል።


ካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ውሉደ ብርሃን እና የሐምቡርግ ደብረ መድኃኒት ኪዳነ ምሕረት መዝገበ ምሕረት ሰ/ት/

ቤቶች መዘምራንም በዓሉን የሚያዘክሩ ዝማሬዎችን በበገናና በክራር ታጅበው አቅርበዋል።


በተለይም በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በሃይማኖቱ ተከታዮች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ በማስመልከት “ኢትዮጵያ ታበጽ

እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር -- ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” እንደተባለ ስለ ቤተ ክርስቲያን፣ ስለ ሀገርና

ስለሕዝበ ክርስቲያን አምላካችን ምረቱን እንዲያወርድ በለቅሶ የታጀበ ምላም ተደርጓል።


እኔ ቅዱስ ነኝና እንደእኔ ቅዱሳን ሁኑ ዘጸ፱፪ የሚለውን የአምላካችንን ቅዱስ ቃል መረት በማድረግም በርሰ ደብር

ሩይ እስጢፋኖስና በካርልስሩኸ ምራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በቀሲስ ጌታቸው

አማካኝነትም ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል።


ገራችን አንዳንድ አካባቢዎች በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ግፍና መከራ በማውገዝም አግዚአብሔር በምሕረቱ

እንዲጎበኘን ያልተቋረጠ ጸሎት ምመኑ እንዲያደርግም መምራኑ አሳስበዋል።


የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የካስል ደ/ቀ/መድኃኔዓለምና የሐምቡርግ ደብረ መድኒት ኪዳነ ምሕረት

አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪ መጋቤ ምሥጢር ዶ/ር ኅሩይ ኤርምያስ ያ ሁሉ የስደት ጊዜ አልፎ ለዚህ በመድረሳችን

ለአምላካችን ክብርና ምስጋና ይድረሰው ብለዋል።


የደብሩን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት እንዲቻል ከባንክ በብድር ተወስዶ ከነበረው ፻፳፼ ሺ ብር ውስጥም ባለፈው አንድ

ዓመት ብቻ ግማሹ መመለሱን የገለጹት አስተዳዳሪው እንዲህ ይነት ተምር የመድኃኔዓለም ፈቃድና ይሁንታ ከሌለበት

እንዴት ይፈማል በማለትም ምመኑ አምላካችንን ደጋግሞ እንዲያመሰግን ጠይቀዋል። ቀሪውንም እዳ በአጭር ጊዜ

በማጠናቀቅ በሌሎች ከተሞች ተመሳሳይ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነፁ መላው ምመን ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም

በእግዚአብሔር ስም ጠይቀዋል።

መናኑም ጥያቄውን በመቀበል የቻሉትን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ በጭብጨባና በልልታ ቃል ገብተዋል።


ቅዳሜ ከቀኑ 10፡00 (17፡00) በዋዜማ ቁመት የተጀመረውና ማምሻውን በትምህርተ ወንጌል ሌሊቱን በማኅሌት ቀጥሎም

በቅዳሴ፣በምሕላና በዑደተ ታቦት የተከናወነው የበዓሉ መርሐ ግብር በመሳጭ ማኅሌቱ፣ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ቅኔ

በምእመናንም እልልታና ጭብጨባ ታጅቦ ን በሐሤት የሞላ ድንቅ በዓል ሆኖ አልፏል


ደብሩን በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤና በሕንፃ አሪ ማበሩ ውስጥ ለሁለት የምርጫ ያት ላገለገሉት የአመራር

አባላት የምስክር ወረቀትና የማስታወሻ ሽልማት በደብሩ አስተዳዳሪ ተበርክቷል። ምእመኑም ከመቀመጫው ተነ

ቤተ ክርስቲያኑን በቅንነት ላገለገሉት አመራሮች በእልልታና በጭብጨባ ምስጋናውን አቅርቧል።


በደብሩ አስተዳዳሪ የተዘጋጀውና የመጀመሪያው እትም ሽያጭ ሙሉ ገቢ ለቤተ ክርስቲያኑ ሕንፃ የባንክ እዳ ለመመለስ

ለሚሰባሰበው ገቢ እንዲውልም “ቅዳሴ ርባን” የተሰኘው መንፈሳዊ መጽሐፍ ለገበያ ቀርቧል። ደብሩ የሕንፃ ቤተ

ክርስቲያንባለቤት ለመሆን በመብቃቱም “ቀራንዮ መጽሔት ታትሞ በመጠነኛ ዋጋ ለምመኑ መራጨት ጀምሯል።

መናን አላማውንከማሳካት ባሻገር ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ጥንካሬ የሚጠቅሙንን መጽፍና መጽሔት በማንበብ

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና በእምነታችን ፀንተን እንድንኖርም አስተዳዳሪው አስገንዝበዋል።


በመጨረሻም ታቦተ ሕጉ ዑደት በማድረግ የበዓሉ ሥነ ርዓት በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል። የተባረከ መስተንግዶ

በመደረጉም ምመኑ ምስጋናውን አቅርቧል።

 

Last Updated on Saturday, 16 November 2019 12:22
 
የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በካስል ከተማ በድምቀት ተከበረ። PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Saturday, 19 January 2019 12:40

ጥር ፲፩- ፳፻፲፩ ዓ.ም (ካስል-ጀርመን)የጌታችን የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በተረኛው ደብር በካስል ደብረ

ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በእለተ ቀኑ በድምቀት ተከበረ።


በበዓሉ ላይ የካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም፣የሀምቡርግ ኪዳነ ምሕረት፣የካርልስሩኸ ምእራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣

የብሬመን ቅዱስ እስጢፋኖስ፣የዳርምሽታት ኪዳነ ምሕረትና የሩዘልስሃይም መጥምቁ ዮሐንስ አብያተ ክርስቲያናት ታቦታትና ምዕመናን

ተሳትፈዋል። ትናንት አመሻሹ ላይ የጀመረው የከተራው በዓል በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሊቃውንት አባቶችና መዘምራን ጥዑመ ዜማዎች

ታጅቦ ለአካባቢው ልዩ ድባብ ሰጥቶታል።


ታቦታቱ ወደ ማደሪያቸው በተንቀሳቀሱበትም ሆነ ወደ ማረፊያ ስፍራቸው በሚመለሱበት ጊዜ በከተማዋ የሚገኙት የአገሬው ነዋሪዎች

በስነ ስርዓቱ በመደመም ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊቶች ገለፃ እንዲደረግላቸው እንደገፋፋቸውም ለማወቅ ተችሏል።


የጥምቀት በዓልን አብያተ ክርስቲያናቱ በዙር በጋራ ላለፉት ስድስት ዓመታት ሲያከብሩት የነበሩ ሲሆን ፤በቤተ ክርስቲያን አባቶች

አንድነት ምክንያት አዲስ አደረጃጀት በመምጣቱ ቀጣዩ አዘጋጅ ደብር ለጊዜው እንዳልተወሰነም ነው የተነገረው።


የጥምቀቱ በዓልም ከትናንት እኩለ ለሊት ጀምሮ በማሕሌት፣በዝማሬ፣በወንጌል ስብከትና በቅዳሴ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 3 ሰዓት ላይም የፀበል ቡራኬና ርጭት ተካሂዶ ታቦታቱ ካደሩበት ስፍራ ተነስተው

በደማቅ ስነ ስርዓት በምዕመኑ ታጅበው ወደየመጡባቸው አካባቢዎች ተሸኝተዋል።


በዓሉን አስመልክተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የተረኛው ደብር አስተዳዳሪ መጋቤ ምሥጢር ህሩይ ኤርምያስ

ለበዓሉድምቀት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉትን አድባራትና ምእመናን አመስግነዋል።በተለይም ከፍተኛ ብርድና በረዶ በሚዘንብበት

በአሁኑ ወቅት ከሩቅ አካባቢ የመጡት አድባራት አባቶችና ምዕመናን የተዋሕዶ ሃይማኖት እምነት ፅናት መለኪያዎች ናቸው

ነበር ያሉት።


የበዓሉ አከባበር ወደፊት በጋራ በደመቀ ሁኔታ እንደሚቀጥል ተስፋ እንዳላቸውም አስተዳዳሪው አስታውቀዋል።

በበዓሉ ላይ የተሳተፉት ምእመናንም በበዓሉ ድምቀት መገረማቸውንና አገር ቤት ያሉ ያህል እንደተሰማቸው ለዚህ ዜና ዘጋቢ

ነግረውታል። የካስል ደብረ ቀራንዮ መድሃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የራሱን ሕንፃ በባንክ ብድር ጭምር የገዛ በመሆኑም ምዕመናኑ

የበኩላቸውን የገንዘብድጋፍ አድርገዋል። ወስብሃት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!

 

Last Updated on Saturday, 19 January 2019 14:00
 
የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በደብራችን አዘጋጅነት በድምቀት ይከበራል። PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Saturday, 29 December 2018 18:53

የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በደብራችን አዘጋጅነት በድምቀት ይከበራል።

 

ካስል ታህሳስ ፲፱ /፳፻፲፩ ዓ.ም (ጀርመን) የዘንድሮው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በርካታ

አድባራት በተገኙበት በካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እንደሚከበር ተገለጸ።


የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መጋቤ ምሥጢር ኅሩይ ኤርምያስ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት በዕለተ ቀኑ በጀርመን

ሀገር በካስል ከተማ በሚከበረው በዚሁ በዓል የሐምቡርግና የዳርምሽታት ኪዳነ ምሕረት ፣የካርልስሩኸ ምዕራፈ ቅዱሳን

አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ የብሬመን ቅዱስ እስጢፋኖስና የሩሰልስሃይም መጥምቁ ዮሐንስ አብያተ ክርስቲያናት

ማኅበረ ካህናትና ምእመናን ይሳተፋሉ።

ፎቶ- በተወዳጅ

በዓሉን እንደወትሮው የተሳካ ለማድረግም ከወዲሁ ተረኛው ደብር ካስል መድኃኔዓለም የተለያዩ ኮሚቴዎችን በማቋቋም

እንቅስቃሴ መጀመሩንም አስተዳዳሪው አስታውቀዋል።


በዓሉ በዕለተ ቀኑ አርብ ጥቅምት ፲ እና ፲፩ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም (January 18&19 - 2019) ሲከበር በከተራው ቀን በጀርመን

ሰዓት አቆጣጠር ከ፲፯ ሰዓት ጀምሮ የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች እንደሚኖሩም ነው የተጠቆመው።


በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረትም ታቦታቱ ወደ ተዘጋጀው ጥምቀተ ባሕር ወርደው ሌሊቱን በሥርዓተ ማኅሌቱ

እና ቅዳሴ ስብሐተ እግዚአብሔር ሲቀርብ አድሮ ከዚያም ንጋት ላይ የጥምቀተ ባሕር ቡራኬው ተካሂዶ ከተጠናቀቀ

በኋላ ወደየመጡበት ደብር በክብር እንደሚሸኙ የተያዘው መርሐ ግብር ያመለክታል። 

ፎቶ- በተወዳጅ

ከዚህ ቀደም ቢበዛ አራት አብያተ ክርስቲያናት እየተሳተፉበት በዙር ሲካሄድ የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ

ክርስቶስ የጥምቀት በዓል ዘንድሮ አምስት አብያተ ክርስቲያናትና አንድ እጩ ቤተ ክርስቲያን ስለሚሳተፉበት ብሎም ደብሩ

የራሱን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንበገዛ በት ማግስት መከበሩ ልዩ እንደሚያደርገውም ነው አስተዳዳሪው የተናገሩት።


የካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ከ፪፻ሺ በላይ ዩሮ ወጪ የራሱን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ገዝቶ

ካለፈው ጥቅምት መድኃኔዓለም ጀምሮ ለአገልግሎት ማብቃቱ ይታወሳል።


ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!

 

 

Last Updated on Saturday, 29 December 2018 19:26
 
የስኬታችን ምስጢር- መድኃኔዓለም PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Friday, 30 November 2018 21:00

 

የስኬታችን ምስጢር- መድኃኔዓለም

 

በደብሩ ሚዲያ ክፍል

 

የካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አመሠራረት ረጅም ጊዜ የወሰደ ሲሆን እንቅስቃሴው የተጀመረው

ከሩብ ክፍለ ዘመን በፊት በጀርመን ሀገር በስደት ላይ በነበሩ እትና ወንድሞች በስደተኞች ማረፊያ ጣቢያ ነው።

የጀርመን ሀገር እምብርት ከሆነችው ካስል ከተማ በ17 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኢመንውዘን ከተማ

ውስጥ በነበረ አንድ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ ተጠልለው የነበሩና መድኃኔዓለም ልባቸውን

ያነሣሣቸው ልጆች በመረቱት የጽዋ ማበር የተጣለው ጅምር መሠረት ዛሬ የራስ ንፃ ቤተ ክርስቲያን

ባለቤት ለመሆን በቅቶ ከተማዋንም ምናኑንም እየባረከ ይገኛል።

 

አባቶች ችግር ካልመጣ የመፍት ሳብ አይፈልቅም እንደሚሉት ከቤተ ክርስቲያንም ከሀገርም ርቀው በስደት

ላይ የነበሩት እት ወንድሞች መሰባሰቢያ ፍለጋ ብሎም አምላካቸውን በእምነታቸው ለማመስገን በማሰብ ነበር

ጽዋ መጠጣት ጀመሩት። ቀስ እያለ ግን የተሻለ የሃይማኖት ውቀ ያላቸው ወንድሞች ለትምህርትና ለተለያዩ

ጉዳዮች ወደ ጀርመን ሲመጡ ምክርና ድጋፍ በመስጠት ጽዋ ማበሩ ከመጠለያ ካምፕ ወጥቶ በተውሶ ወደተገኙ

አብያተ ክርስቲያናት በመምጣት ከከተማው ነዋሪዎች ጋር በጋራ አምላካችን መድኃኔዓለምን ማመስገን ተጀመረ


የምእመኑ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱም ቤተ ክርስቲያን የመመረት ፍላጎ እየጨመረ መጣ። አንድ

ቀራንዮ መድኃኔዓለም አካባቢ (አዲስ አበባ) የመጣ ወንድም ባቀረበው ሐሳብ መሠረት ማኅበሩ ‘የካስቀራንዮ

መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን’ በሚል ስያሜ ይጠራ ጀመር።


በመቀጠልም በወር አንድ ቀን የመድኃኔዓለምን ወርኃዊ በዓል በቅዳሴ ማክበር ተጀመረ። በሰ/ት/ቤት ደረጃ የተቋቋመው

ይኸው ማኅበር ታቦተ ሕግ የገባለትና ወደ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንነት የተሸጋገረው መጋቢት 27 ቀን 2002 ዓ/ም

(ኤፕሪል-2009) በወቅቱ በነበሩት የአውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ እንጦንስ ተባርኮ ሲሆን

ከዚያ በፊት ለስድስት ዓመታት ያህል መልአከ ፀሐይ አባ ሲራክ ወ/ሥላሴ ከፍራንክፈርት ደብረ ፀሐይ

ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ታቦተ ሕግ እያመጡ ወርኃዊው ቅዳሴ ሲቀደስ ቆይቷል።

በወር አንድ ጊዜ ቅዳሜ ሲሰጥ የቆየው አገልግሎ እስከ ታኅሣሥ ወር 2004 ዓ.ም ድረስ በዚሁ መልኩ የቀጠለ ሲሆን

በአሁኑ በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ም/ዋና ራ አስኪያጅ የካስል ደብረ ቀራንዮና

የሐምቡርግ ደብረ መድኒት ኪዳነ ምሕረት አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪ ሆኑት መጋቤ ምጢር ሩይ

ኤርምያስ መምጣት ተከትሎ እንደሌሎቹ አብያተ ክርስቲያናት የሰንበት እሑድ አገልግሎት መስጠት፣ ልደትን፣

ጥምቀትን፣ ስቅለትንና ትንሣኤን ጨምሮ ዓመታዊ በዓላትን ማክበር ተጀመረ። የደብሩም መጠሪያ ስያሜ

በተሟላ ሁኔታ ‘የካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን’ ተብሎ ተስተካክሎ በመንግሥት

እንዲታወቅና የተሟላ የቤ/ክ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ፈቃድ እንዲያገኝ ተደረገ። ይሁን እንጂ

በየጊዜው የሚያጋጥመው የቦታ ችግር አገልግሎቱን በሚፈለገው መጠን ለማሳደግ እንቅፋት በመሆኑ በደብሩ

አስተዳዳሪ ሐሳብ አመንጪነት የራስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት ወይም ለመገንባእንቅስቃሴ

ተጀመረ፣ ይህንኑ ሥራ የሚያስተባብር በደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀ መንበርነት የሚመራ የሕንፃ ግንባታ

ማኅበር በጀርመን ሀገር ሕግ መረት ተቋቋመ።

ከምን ተነን?

ዱ ብለን የተነነው የመድኃኔዓለም ቤትን ለመገንባት እሱኑ አምላካችንን አምነን እሱን ይዘን ነው።

የምንራው የአምላካችንን ቤት በመሆኑም እንደምናሳካው ሙሉ እምነት ነበረን። ቀጥለን ዝባችንም

እንደማያሳፍረን በመገንዘብ መንቀሳቀስ ጀመርን።


የመጀመሪያ ብታችን የሆነችንም የደብራችን አስተዳዳሪ መጋቤ ምሥጢር ኅሩይ ኤርምያስ እ

የቀድሞው የሙኒክ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የአሁኑ የምዕራብ

ወለጋና ቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በመድኃኔዓለም ዓመታዊ በዓል ላይ

በጋራ ያሬዳዊ ዜማና ወረብ በማቅረብ ያሰባሰቡት መነሻ የምመናን የድጋፍ መዋጮ ነበር።

በመቀጠልም በፍራንክፈርት በመስቀል ደመራ በዓል፣ እንዲሁም በፍራንክፈርትና በሽቱትጋርት

በተካሄዱት በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ዝግጅቶች ላይ ሊስትሮ በመጥረግ

ገቢው በሙሉ ለቤተ ክርስቲያኑ እንዲውል ተደርጓል። በመላው ጀርመን የሚገኙ ምእመናን

የአንበሳውን ድርሻ ሲይዙ መጠነኛም ቢሆን የእስልምና የካቶሊክና የወንጌላውያን እምነት

ተከታዮችም የበኩላቸውን ድጋፍ አድርገዋል።


በየአብያተ ክርስቲያኑ የቃል ኪዳን ሰነድ በመፈረምና በባንክ ሂሳብ በመላክ አሁንም ድረስ

የካስልና በጀርመን ሀገር የሚገኙ ብሎም ከአሜሪካ ከካናዳ ከኢትዮጵያ ከሌሎቹም አውሮፓ

ሀገራት በደብራችን ሕንፃ ግዢ ላይ ምመናን እየተሳተፉ ይገኛሉ። ይህ ሁሉ ጥረትና ድጋፍ ነው

ደብሩ የራሱን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት ያበቃው።


እርግጥ ነው በዚህ ሁሉ እንቅስቃሴ ባለፈው አምስት ዓመታት 100 ሺህ ዩሮ ለመሰብሰብ ተችሏል።

ሆኖም ደብሩ ከባንክ 120ሺህ ብር ብድር በመውሰድ ጭምር ነው የራሱ ሕንፃ ባለቤት ለመሆን

የበቃው። ይህንን ያስቻለን አምላክ ዳችንንም ጨርሰን እጃችንን ወደ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት

ለመዘርጋት እንደሚያስችለን ቅንጣት አንጠራጠርም።

ምን ራን?

ከላይ እንደጠቆምነው የሕንፃ /ክኑ የግዢ ዋጋ ቀደም ሲል በተደረገ ድርድር ከፍተኛ ቅናሽ

የተደረገበት ሲሆን ተያያዥ ወጪዎችን ጨምሮ ወደ 220,000,00 ዩሮ ተከፍሎበታል። ከዚህም

ገንዘብ ላይ ደብሩ ለጊዜው መሸፈን የቻለው 100ሺህ ዩሮውን ብቻ ሲሆን ቀሪው 120,000,00

(አንድ መቶ ሃያ ሺህ) ዩሮ በባንክ ብድር የተሸፈነ ነው። ሕንፃው የኢ////ክንን ቅርጽና መልክ

እንዲይዝ 20ሺህ ዩሮ በላይ የሚገመት ለ42 ቀናት ያህል እድሳትና ቀላል የውስጥ ግንባታ ሥራው

ሙሉ በሙሉ በደብሩ ምእመናንና በበጎ አድራጊዎች ተሸፍኗል።

 

የደብሩ ሕንፃ ከካስል ወንጌላውያን ቤ/ክ ላይ በነሐሴ ወር 2010 / በደብሩ ስም ሕጋዊ ውል ተፈርሞ

ተገዝቷል። ከግዢው ውል መፈረም ማግት ጀምሮ በእውነት ቤተ ክርስቲያኑን በሀገር ቤት ካሉት

የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ጋር ለማመሳሰል በከፍተኛ የላፊነት መንፈስ የቤተ ክርስቲያኑ ላፊዎችና

መናኑ ራሳችን መንዲስ፣ ቀያሽ፣ ግንበኛ፣ አናጢ፣ ቀለም ቀቢ፣ ሁሉንም ይነት ባለሙያዎች ሆነን የእኛ

የምንላትን ቤተ ክርስቲያን ርተናል።


በቤተ ክርስቲያኑ እድሳትና ጥገና ዙሪያ እናቶች አባቶች ወንድሞች እቶች ፃናት ሳይቀሩ ተሳትፎ ያደረጉበት ነው።

የመጋቤ ምጢር ሩይ ኤርምያስ የአቶ ሰሞን ሩክና የወ/ት ርብቃ ሚካኤል አመራርና አንቀሳቃሽነት ታሪክ

የማይረሳው ሆኖ ሲዘከር ይኖራል። የጎላ እንቅስቃሴ ስለነበራቸው እነሱን አነሳ እንጂ የቤተ ክርስቲያኑ መንፈሳዊ

አስተዳደርና ሕንፃ ግንባታ ኮሚቴ አባላት ሁሉ ተሳትፎ ከፍተኛ ነበር።


ጥቅምት 24 እና 25/2011 ዓ.ም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ምረቃ

ከጥቅምት 24 /2011 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት በዘለቀው የደብሩ ምረቃ በዓል ላይ ከመላው ጀርመን የሚመጡ

እንግዶችን ለማስተናገድ ጠላ ጠምቀውና ቄጤማ ነስንሰው ሲጠባበቁ የነበሩትን እናቶቻችንና እቶቻችንን ላስተዋለ

በእውነትም የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ መገዛት ሐሴተ ልናን እንመጣ ያረጋገጠ ነበር።


ልጇን የምትድር እናትና ዘመድ አዝማድ ተሰባስቦ እንጀራ ሲጋግር ወጥ ሲወጠውጥና የጎደለውን ለማሟላት ወዲህ

ወዲያ ሲል የማየትን ያህል ይመስል የነበረው ዝግጅት እውነትም አምላችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳንም የዚህ

ስኬት አካል አደረገን በማለት ደጋግመን እንድናመሰግነው አድርጎናል።


በተለይ ከኑረንበርግ መ/ጸ/ቅ ሥላሴ፣ ከቩርስቡርግ መ/ል/ቅ ማርቆስ፣ ካርልስሩኸ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት፣

ከሐምቡርግ ደ/መ ኪዳነ ምሕረትና ከዳርምሽታት ሐመረ ኖ ኪዳነ ምሕረት እንዲሁም ከበርሊን ደብረ ገነት አማኑኤልና

ከክሮንበርግ ደብረ ይል ቅዱስ ራኤል ወቅዱስ ያሬድ አብያተ ክርስቲያናት፣ ከብሬመን ደ/ሰ/ቅ እስጢፋኖስ፣

ከሮሰልስሀይም ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ እንዲሁም ከካስል የኤርትራ ቅዱስ ሚካኤል አ/ክናት የመጡት

ካህናትና ምእመናን ነጫጭ ልብሶቻቸውን አድርገውና መንፈሳዊ ዜማዎችን እያሰሙ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ

ሲገቡ ለተመለከተ ሃይማኖታችን የደመቀችበት ነፍሳችንም በደስታ ብዛት ከሰማየ ሰማያት ደርሳ የተመለሰችበትን

ድባብ ፈጥሯል።


ሁሉም በባለቤትነት ስሜት ያከበረውና ጥረቱ ለፍሬ የበቃበት በመሆኑም ለዚህ ራ መሳካት የቻሉትን ላበረከቱት

የደብ ሥራ አመራር አባላት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ምስጋናውንና አድናቆቱን ሲገልፅም የተስተዋለበት ፍ

ሰላማዊ በዓል ነበር። ከቅዳሜ ከሰዓት በላ ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር የዋለው በዓሉ ሙሉ

መንፈሳዊ አገልግሎቱ ሌሊቱን ሁሉ ሳይቋረጥ ተከናውኗል።


በተለይም በሰንበተ ክርስቲያን/እድ/ ለት ጥቅምት 25 ቀን 2011 / በጀርመን 3ኛው የኢትዮጵያ

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሀብትና ይዞታ የሆነው የካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ

ክርስቲያን አዲስ ሕንፃ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናትና በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ምእመናን

በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።


የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ምሥጢር ኅሩይ ኤርምያስ ለሕንፃ /ክኑ ግዢ መሳካት እሳካሁን ድረስ በገንዘብ፣

በጉልበት፣ በሙያና በዓይነት የረዱትን አጥቢያ /ክናት፣ የጽዋ ማኅበራት፣ የደብሩን / እና የሕንፃ ሥራ

ማኅበር አባላት እንዲሁም በርካታ ምእመናን በሙሉ ያመሰገኑ ሲሆን በቀጣይም የባንክ ዳው

እንዲከፈልና ደብሩን ከማንኛውም ዕዳ ነፃ ለማድረግ ድጋፋቸው እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በዕለቱም ከ10 ሺህ ዩሮ በላይ

ድጋፍ ተገኝቷል።

ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስም የሕንፃ /ክኑ ግዢ የኢትዮጵያን / በጀርመን ሀገር 3 ጊዜ ባለይዞታ ያደረገ አኩሪና ለመላው

ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ ደስታ የሆነ ሥራ መሆኑን በመግለጽ ከደብሩ አስተዳዳሪ ጀምሮ ለሕንፃ /ክኑ መገዛት በተለያየ መንገድ

እገዛና ትብብር ያደረጉትን በሙሉ በሀገረ ስብከቱና በራሳቸው ስም አመስግነዋል።


በበዓሉ የደብሩን የልማት ሥራ መነሻና መድረሻ የሚያሳይ ሥዕላዊ መግለጫም በሕንፃ ሥራ ማኅበሩ /ሰብሳቢ በአቶ

መስፍን አብርሃ ገላጭነት ተሰጥቷል።


በደብሩ ጋባዥነት በበዓሉ ላይ የተገኙት በጀርመን የኢፌድሪ አምባሳደር ኩማ ደመቅሳ እና የኢፌድሪ ቆንስላ ጀነራል

አቶ ምሕረት ሙሉጌታም ምእመናን በመተባበር የሠሩት ይህ ሥራ ሀገር የሚያኮራና የአንድነትና የመተባበርን ጠቀሜታ

አጉልቶ የሚያሳይ ተግባር መሆኑን በመጠቆም /ክኒቱ የበርካታ ዕሴቶች ባለቤት ለሀገርም ከፍተኛ ውለታ

የዋለች እንደመሆኗ መጠን የልማት እንቅስቃሴው በዚህ ሳይገታ በሁሉም ዘርፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል

ተስፋቸውን ገልጸዋል።


የአድባራት አስተዳዳሪዎችም በየበኩላቸው በሥራው መርካታቸውን በመግለጽ ደስታው የጋራችን እንደመሆኑ

መጠን ቀሪውን ዕዳም መክፈል የጋራ ኃላፊነታችን ይሆናል ብለዋል። ከተለያዩ አድባራት የተገኙት በርካታ

ምእመናንም ፍጹም የሆነ ደስታቸውን በእንባ ጭምር ገልጸዋል። በመጨረሻም ታቦተ ሕጉ ወደ ውጭ

ወጥቶ ከቤ/ክኑ ጋር ተያይዞ ባለው ሰፊ ሜዳ ላይ ዑደት ካደረገ በኋላ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

ምን ይቀረናል?

ከላይ በዝርዝር ለመግለ እንደተሞከረው ከሞላ ጎደል የደብሩ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ጥንቃቄ በታማኝነት የተከወነ ነው።

ከእያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚሰበሰበው ገቢ በዝግ አካውንት በማስገባት ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ

ጊዜ ገንዘብ የወጣው የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ግዢ ሲፈም ነው።


ሆኖም አበው እንደሚሉት ምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለኀምሳ ሰው ደግሞ ጌጡ ነውና ልማችንን እውን ለማድረግ

ከባንክ የተበደርነው 120 ሺ ዩሮ ለእኛ ለጥቂቶቹ ሸክም ስለሚሆንብን ዳውን ተከፋፍለን በመክፈል የመድኃኔዓለምን በረከት

ለመካፈል መፍጠን ይገባናል። የደብሩ ሰ/ጉ እና ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ እንደከዚህ ቀደሙ በተከታታይ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ

እቅዶችን ነድፈው ራ መጀመራቸውንም በዚሁ አጋጣሚ ለማብሰር እንወዳለን።


ደብሩ ቀሪውን ለመክፈል ይችል ዘንድ ማገዝ ለምትፈልጉ የደብሩ ሕንፃ አሠሪ ማኅበር የባንክ ሂሳብ ቁጥር

እንደሚከተለው ነው።


Kirchenbauverein Debre Qeraniyo Medhanealem

IBANDE81 5205 0353 0011 8149 26

BICHELADEF1KAS

የልቦናችንን መሻት የሚያውቀው ቸሩ አምላካችን መድኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጀመርነውን ራ አጠናቀን በሌሎች

አድባራት የተጀመሩትን የራስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የመግዛት እንቅስቃሴዎች ለመርዳት ያብቃን። በዚህ አጋጣሚ

ለኢትዮጵያችንም ለሃይማኖታችንም ቅርስ ያኖርንበትን ራ ለማሳካት በተለየ ሁኔታ በሙሉ አቅማችሁ

 

ከጎናችን ሳትለዩ እየራችሁ ላላችሁት ኤርትራውያን እት ወንድሞቻችን ምስጋናችን የላቀ ነው። መድኃኔዓለምም

ድካማችሁን እንዲያስብላችሁ በመመኘት እስከመጨረሻው በፍቅርና በአንድነት አብረን እንደምንዘልቅ እንተማመናለን።

ወስብሃት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር።አሜን!

 

Last Updated on Saturday, 29 December 2018 19:44
 
« StartPrev12345678910NextEnd »

Page 2 of 12

Who's Online

We have 25 guests online

ሌሎች ድረ ገጾች

Featured Links:

feed-image Feed Entries


Powered by Medhanealem.