ምእመናን ቤተክርስቲያናቸውንና ሃይማኖታቸውን የመጠበቅ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተጠቆመ። |
|
|
|
Written by Administrator
|
Sunday, 25 November 2012 18:39 |
በጀርመን አገር አንዲት የእስልምና ተከታይ ከነልጇ ወደ ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖቷ ተመለሰች።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
(ካስል-ጀርመን) ምእመናን ቤተክርስቲያንን ከኑፋቄ አስተምህሮና ሥርዓቷን ከሚፃረሩ ቡድኖችና ግለሰቦች የመጠበቅና የመከላከል አደራና ኃላፊነት እንዳለባቸው በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ አሳሰቡ።
አስተዳዳሪው መምህር ኅሩይ ኤርምያስ ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት ፳፭ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በጀርመን አገር በሚገኘው የካስል መድኃኔዓለም ወርኃዊ በዓል ላይ አንዲት ባለማወቅና በግፊት ከገባችበት የእስልምና እምነት የተመለሰችን እናት ወደ እናት ቤተክርስቲያኗ ለመመለስ የሚያስችላትን ተገቢውን ሥርዓት ከፈጸሙላትና ሕፃን ልጇንም ካጠመቁላት በኋላ የመንፈስቅዱስን ልጅነት መቀበላቸውንና የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ምእመናን መሆናቸውን ለማብሰር በሰጡት ቃለ ምዕዳን በዕለቱ ለተገኙት ምእመናን ከነልጇ ወደ ርትዕትና እውነተኛ ሃይማኖቷ የተመለሰችው እናት ውሳኔ ቤተክርስቲያናችንን በኑፋቄ ትምህርታቸው ለመመረዝ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን የሚመክርና የሚገስጽ መሆኑን ጠቁመዋል።
|
Last Updated on Sunday, 25 November 2012 18:46 |
Read more...
|